Old school Swatch Watches
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

ሙስሊም እህትሺን እንዴት ነው የምትን ከባከቢያት?


Hw 2 treat ur sister 2

የምእራቡ ቁሳዊ ሂወት የመንፈስ መበላሸትን ያበረታታል።ማህበራዊ ትስስር ወይም ዝምድና የሚባለው ነገር ንትርክ የበዛበት፣ግለኝነት እና ከመተባበር ይልቅ ውድድር የሚስተዋልበት ነው።ይህ መገለጫ ባህሪ ኢስላም ከሚያበረታታው መንፈሳዊ ሂወት በተቃራኒ ነው።ኢስላም አማኞቹን ጤናማ የሆነ ማህበራዊ ኑሮን እንዲመሰርቱ፣ለሰወችም ቅርብ እንዲሆኑ፣ዝምድናን እንዲቀጥሉ እና ከግለኝነት ይልቅ ትብብር የተሞላበት ሂወትን እንዲመሩ ያዛል።

አንድ ሙስሊም ሴት እህቶቿን እንዴት ነው የምትንከባከባቸው?

1) ለአሏህ ብላ ትወዳቸዋለች

ይህ ፍቅር በማንኛውም አለማዊ አና ስውር ጥቅም ያልተመረዘ የሆነ ነው።እውነተኛ የእህትነት ፍቅር ከኢስላም መመሪያ ብርሃን የሚመነጭ ግኑኝነት ወይም ማህበሪዊ ትስስር ነው።እንዲሁም አንዲት ሙስሊም ሴትን ጁኦግሪፊያዊ መነሻ፣ጐሳ፣የቆዳ ቀለም፣የአይን ቀለም ወይም የፀጉር ቴክስቸር እና ቇንቇ ሳይገድባት ከእህቶቿ ጋር ልብ ለ ልብ የሚያስተሳስር ብቸኛ ሰንሰለት ነው።ሰንሰንሰለቱም መሰረት ያደረገው የአሏህን(ሱ.ወ.ተ) እምነት ነው።

-<({አል-ቁርአን 49:10})>-

"አማኞች ወንድማማቾች ናቸው።በመካከላቸውም እርቅን ፍጠሩ እናም ምህረትን ታገኙ ዘንድ አሏህን ፍሩ።"

ይህ ፍቅር አንዱ የእምነት ጥፍጥና መገለጫ ነው።

አል-ቡሐሪ ጥራዝ 1 መጽሃፍ 1 የሃዲስ ቁጥር 15
አነስ እንደተረከው
መልእክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) የሚከተሉትን ሶስት ባህሪያቶች ያለው ሰው የእምነት ጥፍጥና ይኖረዋል ብለዋል።
1) አሏህ እና መልእክተኛው ከማንኛውም ነገር በላይ ውድ የሆኑለት
2) ሰውን የሚወድና ውዴታውም ለአሏህ ብሎ የሆነ
3) ወደ ጀሃነም እሳት መወርወርን እንዲሚጠላ ሁሉ ወደ ክፍርና(መጥመምን) የሚጠላ የሆነ

እናም ይህ ፍቅር እውቅናን፣ስልጣንን፣ዝናን እና ክብርን ለማግኘት ተብሎ ያልሆነ ነው።ንፁህ እና ብርሃን የሆነ ቀልብን የሚፈልግ ውዴታ ነው።ከሰው ልብ ጥላቻን ቅናትን እና ባላንጣነትን ለማጥፈት ብቸኛው መንገድ ለአሏህ ብሎ መዋደድ ነው።

3 ደግነትን እና ፍትሃዊነትን ታሳያቸዋለች።

የፍትሃዊነት፣የመልካምነት፣የደግነት ጠቀሜታ ከመቶ ጊዜ በላይ በቁርአን ተገልጿል።የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ በጥንት አማኒያን መካከል በታማኝነት እና በደግነት ተምሳሌት የተሞላ ነበር።

4 ሰላመዊና ሰወዳድ በሆነ ልባዊ እና ፈገግ ባለ ፊት ትቀርባቸዋለች።

በውነቱ የፈገግተኝነት ተግባር የደህንነታችን ስሜት የሚጨምሩ የሆኑ "ኢንዶርፊንስ" እንዲመነጩ ያደርጋል።በትርሚዚ እንደተዘገበው:
እህትሽን በፈገግታ መቅረብ የሶደቃ ተግባር ነው።

5 ለነሱም ቅን ናት።

ቅንነት አንደኛውና ዋነኛው የኢስላም የእምነት ማእከላዊ መርሆ ነው።ቅንነት የሌለው እምነት ዋጋ ቢስ እና ባዶ ነው።
ቡሐሪ ጥራዝ 1 መጽሐፍ 2 የሐሃዲስ ቁጥር 12
ኢብን አነስ እንደተረከው:-

መልእክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) ከእናንተ መካከል ለራሱ የወደደውን ለወንድሙ እስካል ወደደ ድረስ አለመነም ብለዋል።

6 እህቶቿን ችላ አትልም።

ኢስላም እርስ በርስ ወደ መዋደድ፣መተዛዘን፣ወደ ዝምድና ቀጣይነት የሚጣራ ሃይማኖት ነው።እንዲሁም ኢስላም ሙስሊም እህቶችሽን መጥላትን እና ችላ ማለትን የሚከለክል ሃይማኖት ነው።
በቡሐሪ አል-አደቡ አል-ሙፍረድ ላይ እንደተዘገበው
ለአሏህ ብለው ያልተዋደዱ የመጀመሪያው ቅጣት በመሃከላቸው ይመጣል።ከዚህ እና ከሌሎች ሐሃዲሶች መረዳት እንደሚቻለው የተራዘመ ጥላቻ ወይም ኩርፊያ ተቀባይነት አንደ ሌለው ነው።ኩርፊያው ረዘመ ቢባል እስከ ሶስት ቀን ሊሄድ ይችላል።ነገር ግን ከሶስት ቀን ቡሃላ ማብቃት ይኖርበታል።ሃጢያቱ እየሰፋ በመጣ ቁጥር ቅጣቱም ከባድ ይሆናል።ቅጣቱም ባረባ ጭቅጭቅ እና ንትርክ በተለያዩ ሰዋች መሃል ይሆናል።
በሙስሊም እንደተዘገበው መልእክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) ዝምድናን ማቇረጥ እርስበርስ ፊትን በጥላቻ ማዞር፣እርስበርስ መጠላላት፣አርስበርስ መቀናናነት አይኖርባችሁም።አሏህ እንዳዘዛችሁ ወንድማማች ሁኑ ብለዋል።

በቡሐሪ አል-አደብ አል-ሙፍረድ ላይ እንደተዘገበው

ታለቁ ሶሃቢይ አቡደርዳ(ረ.ዐ) ከፆም እና ከሶደቃ በላይ የተሻላችሁን ስለ አንድ ነገር አልነግራችሁምን? በወንድሞቻችሁ መሃል እርቅን አውርዱ፤ጥላቻ ምንዳን ይቀንሳንና ይሉ ነበር።

7 ለነሱ መሃሪም ቻይም ናት።

አንዳንድ ሙስሊም እህቶቻችን በሆነ ነገር መቆጣት ቀላል ነገር መስሎ ሊታያቸው ይችላል።ነገር ግን ትክክለኛ ሙስሊማ ቁጣዋን ትገድባለች፤ለእህቷ ይቅርታ ለማድረግ ፈጣን ናት።ይህን በማድረጔ በሷ ላይ ምንም እፍረት አይታይባትም።ይልቅ ይህን የምትረዳው ለነዚያ መልካም ሰሪ ለሆኑ ብቻ የሚሰጠውን የአሏህን ፍቅር ለማግኘት እና ወደ እርሱም ቅርብ የሚያደርጋት አንድ መልካም ስራ መሆኑን በማሰብና በመረዳት ነው።

-<({አል-ቁርአን 3:134})>-

"እነዚያ ንዴታቸውን የሚገድቡ እና ለአሏህም ብለው ሁሉንም ሰው ይቅር ያሉ እነርሱ መልካም ሰሪዎች ናቸው።"

8 ስለ እነሱም አልቧልታ ወግ ወይም ሃሜትን አታወጋም።

አማኝ የሆነች ሴት ሙስሊም እህቷን አታማም፤አሉቧልታ ወግም አታወራም።ያሉቧልታ ወግም በቁርአን ሃራም እንደሆነ ታውቃለች።

-<({አል-ቁርአን 49:12})>-

"በእርስበርሳችሁ ጀርባ መጥፎ ነገርን አትናገሩ፤ከእናንተ መካከል የሙት ወንድሙን ስጋ መብላ የሚሻ አለንዴ? አትጠሉትምን! አሏህን ፍሩ! አሏህ ተውበትን ተቀባይ ሁሉን መሃሪ ነው።"

አማኝ ሴት ምላሷን ትቆጥባለች እናም ስለ እህቷ መልካም የሆነውን ታወጋለች
መልእክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) እንቶ ፈንቶ ወግ ምን እንደሆነ ታውቃለችሁ ሲሉ ጠየቁ።የተሻለውን አሏህ እና መልእክተኛው ያውቃሉ አሉ፤ወንድማችሁ የሚጠላው ስለሆነ ነገር ማውራት ነው ብለዋል።ስለ ወንድሜ ያወራሁት ነገር እውነት ከሆነስ? ተብለው ተጠየቁ እውነት ከሆነ ስለ እሱ አውግተሃል እናም ውሸት ከሆነ አምተኸዋል። {ሙስሊም}

ሁለት ገፅታ ያለው(ሙናፊቅ) መሆን የዚሁ ክፍል ነው።በእውነቱ ሁለት ገፅታ ያላቸው ሰዋች ከአሏህ ዘንድ በጣም መጥፎ ሰዎች ናቸው።መልእክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) በትንሳኤ ቀን ከአሏህ ዘንድ መጥፎ የሆኑ ሰዎች መካከል ታገኛላችሁ አንደኛው አንዳንድ ሰዋችን በአንድ መንገድ ሲቀርብ ሌሎችን ደግሞ በሌላ መንገድ የሚቀርብ ሙናፊቅ ነው ብለዋል።
{አልቡሐሪ እና ሙስሊም}

8 ቃልኪዳን ማፍረስን፣ስሜት የሚጐዳ የሆነ ቀልድ መቀለድን እና ንትርክን ታስወግዳላች።

በአል-ቡሐሪ አል-አደብ አል-ሙፍረድ ውስጥ እንደተዘገበው
መልእክተኛው(ሰ.ዐ.ወ.) ወንድሞቻችሁ ጋር አትነታረኩ፣አትጨቃጨቁ ከእርሱም ጋር ቅጥ ባለፈ መልኩ አትቀላለዱ፤የምታፈርሱት የሆነን ቃልኪዳንም አትግቡ ብለዋል።

ንትርክ ወደ በለጠ አለመግባባት እና ድርቅና ያመራል፤ለኢብሊስም ክፍት ቦታ ይፈጥራል። አብዛሃኛውን ጊዜ ስሜትን የሚጐዳ የሆነ ቀልድ ጥላቻ እና ክብር ማጣትን ያስከትላል።ቃልኪዳንን ማፍረስ ሰዎችን ሲያበሳጭ በመካከላቸው የነበረውንም ፍቅር ጥላሸት ይቀባዋል።የሚያቆራርጥን ነገር ላለመናገር ማፈግፈግን መማር ይኖርብናል።አንዳንዴም ችግሩ የተሻለ እውቀት ባለው ሰው እስኪፈታ ድረስ "ላለመስማማት መስማማት" ይኖርብናል።የተለያዩ የአካል እንቅስቃሴዎች እና በነሱ የሚደረጉ ምልክቶች ለምሳሌ ጣትን መቀሰር፣ጥርስን መንከስ ወዘተ አለመግባባትን እና ጥላጫን ስለ ሚፈጥሩ ተያቸው፤ከዚህም ልትርቂ ይገባል።

9 ለእህቶቿ ራሷን መሱአት ታደርጋለች።

ሙስሊም ሴት ከካፊር ይልቅ ከሙስሊሞች ጋር ያላትን ጉድኝት ትመርጣለች።የተለመደው የእምነቷ ሰንሰለት ለስብእናዋ እና ለኢስላማዊ ባህሪዋ መሰረት ይፈጥራል።

10 እህቶቿ በሌሉበት ትፀልይላቸዋለች

ቅን የሆነች ሙስሊም ሴት ለራሷ የወደደችውን ለእህቶቿም ትወዳለች በሌሉበት መፀለይን አትረሳም።ይህ ደግሞ የእህትነት ፍቅርን ተግባራዊነት ማሳያ ነው።የዚህ አይነቱ ቅን እና ንፁህ የሆነ ፀሎት በፍጥነት ከሚመለሱት የዱአ አይነቶች ነው።

በቡሐሪ አል-አደብ አል-ሙፍረድ ውስጥ እንደተዘገበው
በፍጥነት የሚመለሰው ዱአ ወንድሙ በሌለበት በሩቅ የሚደረግ ዱአ ነው።

11 እህቶቿን አሏህን የሚያስደስት የሆኑ ነገሮችን እንዲሰሩ ታበረታታቸዋለች።


ዝግጅት: በ ፋጢማ ጃክሰን
© የአማኛ ትርጉም ቅንብር: በ አህመድ የሱፍ
2005


1032

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ